በየዓመቱ ሰኔ 12 የሚከበረው የቅዱስ ሚካዔል የመታሰቢያ በዓል በሲያትል ደብረ ሠላም ቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ:: በበዓሉ ላይ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እንዲሁም ከተለያዩ ስቴቶች የመጡ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ተገኝተዋል::
በዓሉ ቅዳሜ በዋዜማ ቁመት ተጀምሮ፣ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በማህሌት እና በመዝሙር በመቀጠል፣ እሁድ ዕለት በደመቀ ሁኔታ በቅዳሴ፣ በመዝሙር እና በትምህርት ተከብሮ ውሏል::
የዚህን ዓመት ክብረ በዓል ልዩ የሚያደርገው በአዲሱ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን መከበሩ እና በበዓሉ ላይ እጅግ ብዙ አባቶች እና መእመናን ከአጥቢያውና ከተለያዩ ስቴቶች በመሰባሰብ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ በዑደት በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ነው::
የበዓሉን አከባበር በፎቶ ለማየት ይህንን የጫኑ::